Updated and News Updated and News

ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ውጤታማነት የህዝብ ክንፍ አባላት ቅንጅታዊ ትግበራ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተጠቆመ

ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ውጤታማነት የህዝብ ክንፍ አባላት ቅንጅታዊ ትግበራ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተጠቆመ

በፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ልማት ኤጀንሲ በማስፈፀም አቅም ግንባታ ዘርፍ አዘጋጅነት በኤጀንሲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው የምክክር መድረክ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን አቅም ለማሳደግና ውጤታማነታቸውን ለማረጋገጥ የህዝብ ክንፋ አባላት ቅንጁታዊ ትግበራ አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል፡፡  

 

 

 

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አስፋው አበበ የምክክር መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ለሚደረገው ኢኮኖሚያዊ ሽግግር የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ዘርፉን በበቂ ሁኔታ መደገፍና ማስፋፋት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ እያንዳንዱ የህዝብ ክንፍ አባላት ካለው የህዝብ ውክልና አንፃር በዘርፉ ትግበራ ዙሪያ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየትና መፍትሄዎችን በማመላከት ረገድ ትልቅ ሃላፊነት አለው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ከዘርፉ አስፈፃሚ አካላት ጋር በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ዳር 23/2009 ዓ.ም በተካሄደው የህዝብ ክንፍ የምክክር መድረክ የኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር የቀረበ ሲሆን የኢንዱስትሪ ዘርፉ በዋናነት በግሉ ዘርፍ የሚመራ፣ ግብርናን መሰረት ያደረገ፣ ኤክስፖርት-መር የሆኑና ስትራተጂክ ምርቶችን የሚተካ፣ ጉልበትን በዋናነት የሚጠቀሙ ቀላል ኢንዱስትሪዎች ላይ ትኩረት የሚያደርግና የአገር ውስጥና የውጭ ባለሀብትን አቀናጅቶ የመጠቀም አቅጣጫን መሠረት አድርጎ የተዋቀረ እንደሆነ በስትራቴጂው በዝርዝር ተብራርቷል፡፡

 

ሌላው በ2009 የኤጀንሲው እቅድ በዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችና ግቦች ላይም መድረኩ በስፋት ተወያይቷል፡፡ በእቅዱ ዙሪያ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ተብለው በተሳታፊዎች ከተነሱ ነጥቦች መካከል የተመቻቹ የድጋፍ ማዕቀፎች በትክክል ተግባር ላይ እንዲውሉ ከላይ እስከታች ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ቢሰራ፣ የድጋፍ አሰጣጡ በስፋት ወጣቶችንና ሴቶችን ታሳቢ ያደረገ ቢሆን፣ የሽመና ኢንዱስትሪውን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለመደገፍ ጥረት ቢደረግ፣ ህብረተሰቡ የሀገር ውስጥ ምርቶችን እንዲጠቀም አመለካከት የመቀየር ስራ መሰራት ቢችል የሚሉት ዋና ዋናዎች ነበሩ፡፡

Image